ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
102

ቁጥር 01/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን  በድጋሜ  በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ፣ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ  ብር 300 /ሶስት  መቶ ብር/ በመግዛት  አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106  መዉሰድ  ይቻላል፡፡   የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት የራሳቸዉን ቴክኒክ ሰነዶችን በማዘጋጄት  በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ  በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጄዉ የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ  ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ዓይነት ፣ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here