በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች አገልግሎት የሚዉል የጭነት የመኪና ኪራይ ባሕር ዳር ደርሶ መልስ ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ጭኖ ለማምጣት እና መድኃኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመኪናውን ሊቭሪ (የባለቤትነት ማረጋገጫ) ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት ሚውል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባሕር ዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት የሚችሉ፡፡
- የመድህን ኢንሹራንስ ውል ያላቸው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በመተማ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን ከ 21/11/2017 እስከ 05/12/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 06/12/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው እና በሰነዱ ላይ ሥም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም /ሲፒኦ/ ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጭነቱ አይነት በቢያጆ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባሕር ዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚሄደበት ቀን በመብራት መጥፋት ምክኒያት ወይም በወረፋ ምክኒያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል