ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለእ/ሳ/ም/ወ/ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት ለቦረቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚያስገነባው ግንባታ ማለትም፡- ሎት 1 አንድ ብሎክ የቤተ-ሙከራ ግንባታ ፣ሎት 2 አንድ ብሎክ የቤተ መጽሀፍት ግንባታ ፣ሎት 3 አንድ ብሎክ የመምህራን መጸዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 22 ተኛው ቀን 4፡00 ድረስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የግንባታ ሥራ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በማካተት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም ፣አድራሻ ፣ፊርማ ፣ማህተም በማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ ብሔራዊ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታ በ22ኛው ቀን እስከ 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ አንድ ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በስልክም ሆነ በአካል አቤቱታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ በሎት 1 አንድ ብሎክ የቤተ-ሙከራ ግንባታ ብር 46,765 (አርባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አምስት ብር) ፣በሎት 2 አንድ ብሎክ የቤተ መጽሀፍት ግንባታ ብር 31,100 (ሰላሳ አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር) በሎት 3 አንድ ብሎክ የመምህራን መጸዳጃ ቤት ብር 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር) ሆኖ የቫት ተመዝጋቢ ተወዳዳሪዎች ከሆኑ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከነቫቱ መሆኑን እና እንደ ተጫራቾች ምርጫ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ጥሬ ገንዘቡን በመሂ/1 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የግንባታ አይነት በሎት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. .የተቋራጩ ደረጃ BC ወይም GC 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝርመረጃ ማግኘት ከፈለጉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 666 00 03 /058 666 04 14 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  14. ሎት 1 = 6 ገጽ የሥራ ዝርዝር እና 3 ገጽ የዲዛይን ዝርዝር ገጽ የተያያዘ መሆኑን ተጫራቾች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ሎት 2 = 4 ገጽ የሥራ ዝርዝር እና 9 ገጽ የዲዛይን ዝርዝር ገጽ የተያያዘ መሆኑን ተጫራቾች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. ሎት 3 = 5 ገጽ የሥራ ዝርዝር እና 9 ገጽ የዲዛይን ዝርዝር ገጽ የተያያዘ መሆኑን ተጫራቾች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here