ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

ቁጥር 02/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቤተመጻሕፍት ግንባታ ለማሰራት የህንጻ እና ጠቅላላ ተቌራጮችን ከደረጃ 7 እና በላይ   የሆኑ የሚሳተፉበት በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ  የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር የምትቸሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የስራና ከተማ ልማት የደረጃ ማረጋገጫ ሰርተፌኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 /ሃያ አንድ/ ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ድረስ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106፤ በ500 /አምስት መቶ/ ብር ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በኮርፖሬሽኑ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የግንባታ ስራዉ ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ በሚወስደዉ አስፓልት ፤ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here