ሩሀ በሔራዊ ፓርክ

0
60

ሩሀ ብሔራዊ ፓርክ በታንዛኒያ  በ1964 እ.አ.አ ነው የተመሰረተው፡፡ ፓርኩ ከአገሪቱ ሁለተኛ ከአፍሪካ ሶስተኛ ደረጃ ላይ  ነው የሚገኘው – በስፋቱ፡፡ ለፓርኩ በቅርበት የምትገኘው ከተማ ኢሪንጋ ትሰኛለች፤ ርቀቷም 130 ኪሎሜትር ነው።

የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 20,226 ኪሎሜትር ስኩዌር  ተለክቷል፡፡ ሩሀ የሚለው የፓርኩ መጠሪያ በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ከሚፈሰው ሩሀ  ወንዝ የተወሰደ ነው፡፡

 

ሩሀ ፓርክ ለመድረስ ከኢሪንጋ ከተማ ተነስቶ በኮረንኮንች ጐዳና በተሽከርካ፤ አሊያም ባሉት ሁለት የግል የዓየር ማጓጓዣ ድርጅቶች አማካይነት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

በፓርኩ ከሚገኙ የዱር እንስሳት አንበሳ፣ አቦሸማኔ፣ የአፍሪካ ነብር፣ የዱር ውሻ፣ ቀጭኔ፣ ጉማሬ፣ ጅብ፣ ጐሽ እና የሜዳ ፍይል ይጠቀሳሉ፡፡ ከዓእዋፍ 571 ዝርያዎች እንደሚገኙም ተረጋግጧል፡፡

 

በፓርኩ ክልል የሚገኘው ብቸኛው የጐብኚዎች ማረፊያ የሩሀ ወንዝ  ነው፡፡ የዱር አራዊቱ ውኃ ለመጠጣት ከየአቅጣጫው ሲሰባሰቡ በሩሀ ማረፊያ በረንዳ ላይ ሆኖ መመልከት ይቻላል፡፡

 

የፓርኩ ክልል የዓየር ንብረት ከግንቦት እስከ ጥቅምት ደረቅ እና ሞቃት ሲሆን እነዚሁ ወራት ዝናብ የማይጥልባቸው ናቸው፡፡ የቀጣናው  የዓየር ሙቀት ከፍተኛው 35 ዝቅተኛው 20 ዲግሪ ሴልሺየስ ተለክቷል፡፡ በነዚህ ወራት በፓርኩ የሚገኙ እፅዋት የሚጠወልጉበት የወንዞች ፍሰት በእጅጉ የሚቀንስበት ወቅትም ነው፡፡

 

በመልካምድራዊ አቀማመጡ ወጣገባ፣ ኮረብታ፣ ሸለቆዎች ለጀብደኛ ጐብኚዎች በረሀማ ቀጣናንም አካቶ ይዟል፡፡

ፓርኩን ከጐበኙ ከፍተኛው  ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት 2012 እ.አ.አ አቆጣጠር ሲሆን ብዛታቸውም 21,267 ነበር፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት አሲሊያ አፍሪካ፣ ትሪኘ አድቫይዘር ድረ ገፆችን እና ዊኪፒዲያን ተጠቅመናል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here