በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ. ሙሉቀን ዘውዴ ፣2ኛ. ደረጀ አድማስ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 በሰሜን አለነ ዳርጌ ፣በደቡብ አስረሳች ከበደ ፣በምሥራቅ ክፍት ቦታ እንዲሁም በምዕራብ መንገድ የሚያዋስነው በ1ኛ ተከሳሽ ሙሉቀን ዘውዴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ 2‚652‚691.1 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሀምሳ ሁለት ሽህ ስድስት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከአንድ ሳንቲም/ ሆኖ የጨረታ ማስታወቂያው ከሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 አስ/ግቢ ውስጥ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስ/ከፍ/ቤት