በባሕር ዳር ከተማ የፋሲሎ ክፍለ ከተማ የውሃ ቱቦ ፣የውሃ ሆዝ እና በመስመር ጤፍ መዝሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን እቃ በአካል ፋሲሎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በመምጣት ማየት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 9 በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጠ.ድምር /በሎት/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር /ዕቃ/ ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 / አስር ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መ/ሂ1 በማስያዝ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተለየ በኃላ አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፋሲሎ ክፍለ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው አከፋፈት ቅሬታ ያለው ተጫራች ካለ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ባለው 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 15 66 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
የፋሲሎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት