ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳዳር የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዩን የተወሰነ የፕስትሪ አካዉቲግ ስልጠና ፕስትሪ ሶፍትየር ለመጫን እና እንዲሁም ኮምፒዉተሮቹን ለማገናኘት የኔትወርክ ዝርጋታ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና ማሰጫን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት(Tax Payer Identifican NuNber) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዩን የተወሰነ ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኘበት በ11ኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን የጨረታ ማስገቢያዉና የመክፈቻዉ ስዓትና ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ የሥራ ስዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸዉና በታወቁ ባንኮች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው ሁለት ቀን በፊት በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨታዉን ካሸነፉ ለዩንዩኑ ሰራተኞች ስልጠናዉን በ15 ቀን ዉስጥ ስጥተዉ ከጨረሱ በኋላ የባለሙያዎችን አቅም የበለጠ ለማዳበር ለ3 ወር የኦን ላን ስልጠና የሚሰጡ መሆኑን ጭምር መገንዘብ አለባቸዉ፡፡
  9. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነት የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 11 73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዩን የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here