የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት ለስልጠና ፣ለቢሮ አገልግሎት እና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የህንፃ መሳሪያ ፣ሎት 2. ብረታ ብረት ፣ሎት 3. ኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት 4. የእንጨት ውጤቶች እና ኤምዲኤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚዙት ዕቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ሆኖ የጨረታ ሰነዱን እንጅባራ ፖ/ቴ/ኮሌጅ የማይመለስ የአትዮጵያ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በመሂ/1 ወይም በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾቹ የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያ ቅጹን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱን በመግዛት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛዉ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም በተደረገው የጨረታ አከፋፈት ስርዓት ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሲፈልጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 02 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ላይ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእንጅባራ ፖ/ቴ/ኮሌጅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት /በጥቅል/ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል /በአይነትም/ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸፈውን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ ኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ