ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

የጨረታ ቁጥር አካ/ደ/ጥ/ባ KFW 001/2017

በጀርመን መንግስት የልማት ትብብር ባንክ /KfW/ የደቡብ ወሎ ደን ልማት እና ብዝሀ ህይወት ሀብት ጥበቃ ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት እና የቀጣይ ሁለት በጀት ዓመት 2018 ፣2019 የኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡  ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ፡፡
  2. የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ፤የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የሙያና የንግድ ፈቃዳቸውን  ያሳደሱ፡፡
  4. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)፡፡
  5. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው በአብክመ የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
  6. የጨረታውን ሠነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች የምድር ወለል /ግራውንድ/ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ  ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በባንክ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ አብረው ማቅረብ አለባቸው የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 10 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ በ16ኛው ቀን በመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 14 አጠገብ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲገባ መደረግ አለበት ጨረታው በዚያው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  10. ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ሥም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  11. ከብር 200‚000 / ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ አካ/ደ/ጥ/ባ የምድር ወለል /ግራውንድ/ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 62 06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ባ/ዳር ቀበሌ 08 ጋምቢ ቲችንግ ሆስፒታል አጠገብ፡፡

የአብክመ አካባቢ ና የደን ጥበቃ ባለስልጣን

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here