ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

0
45

በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ4ቱም ፑል ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያ ፣ለግብርና ል/ጽ/ቤት አገለግሎት የሚወል ፣ሎት 2 የአቮካዶ ዘር ከነስጋው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለዉ መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000 (ሶስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ28/11/2017 ዓ.ም እስከ 13 /12/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታዉ በ13/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜዉ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየዉ በሎት /በድምር ዋጋ ነዉ/፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
  10. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት በሎት 1 የተጠቀሰውን የመኪና ጎማ ከነከለማደሪያ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት  እንዲሁም በሎት 2 የተጠቀሰውን የአቮካዶ ዘር ከነስጋው ከሐይቅ ከተማ 7 ኪ/ሜትር ከሚገኘው ጃሪ ችግኝ ጣቢያ ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  13. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  14. ጨረታዉን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here