ቁጥር ውአገ/14699/5/35
የደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ድርጅት የ2017 በጀት አመት አቅርቦቶችን ሎት 1. የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች ፣ሎት 2. ከ2014 ዓ/ም እስከ 2017 ዓ/ም የሂሳብ ምርመራ አዲት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያቁጥር /ቲን /ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃወችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከገ/ግ//ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጂዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለመካነ ኢየሱስ ከተማ ውሃ አገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይችላሉ ፤በዚው ቀን 11፡00 ጨረታው ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 8 በ16ኛው ቀን 4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 03 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ድርጅት