ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሰራተኞች ሰርቪስ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የመኪና ኪራይ ለመከራየት በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅቱ ውል ይዞ በየወሩ እየከፈለ ከመስከረም ወር ጀምሮ ለ10 /አስር ወራት/ ተከራይቶ አገልግሎት ማሰጠት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የመኪና አከራይ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት /ሊቭሪ/ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለት ሙሉ ስም፣የድርጅቱ ማህተም፣አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ከነሐሴ 5/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የምንከራየውን ተሸከርካሪ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- አሸናፊው ከጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሰው የሥራ ስዓት ውጭ የግል ስራቸውን የማከናወን መብት አላቸው፡፡
- የውል ጊዜው ሲያበቃ በአከራይና ተከራይ የጋራ መግባባት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተጨማሪ ጊዜ የሚራዘም ይሆናል፡፡
- ለተሸካርካሪው የሚያስፈልጉ የነዳጅ፣የዘይትና ቅባት፣የጎማ፣የሹፌር፣ የጥገናና ሌሎች ወጭ በአከራይ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበባቸው መሆን አለበት፡፡
- ተሸከርካሪው ወደ ሥራ ሲገባ ደህንነቱ በባለሙያ ተፈትሾ ሥራ የሚጀምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል ፤ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመ/ቤታችን ዋና ገ/ያዥ ማካኝነት በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ክፍያ በሚፈጸምበት ወቅት በስማቸው (በድርጅቱ) የተሰራ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከአማካይ የገቢያ ጥናት ዋጋ በላይ የሞላ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 22 23 10 87 /09 18 22 05 04/ 09 18 21 06 28 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል