ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በሰሜን ጎጃም አስተዳደር ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 G+3 የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ሥራ ግዥ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፤እቃው /የግንባታው ግዥ መጠን  ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነና የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ  የምስክር ወረቀቶችን ከዋጋ ማቅረቢያዉ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ለመሬት ሃብት ቆጠራና መዝግቦ ፋይሉን የማደራጀት /በጂኦስፓሻል ዘርፍ /ሥራ ደረጃ 1/ አንድ ከዚያ በላይ እና G+3 የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ሥራ ህንፃ ሥራ ተቋራጭነት እና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 3 (ሶሰት) ከዚያ በላይ ተጫራጮች  በተራ ቁጥር 1 በተጨማሪ የሆነ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፉ 2 /ሁለት/ እና ከዚይ በላይ የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና የሰሩበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 1 እና ሎት 2 በተከታታይ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት ድረስ ለዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሁሉም ሎቶች ማለትም ሎት 1 አና ሎት 2 ለ 30 (ሰላሳ) ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በጋዜጣ ይቆይና በ31ኛው (ሰላሳ አንደኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ላይ ጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ይከፈታል፡፡
  6. በመሆኑም በእለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ለሎት 1 እና ለሎት 2 የመወዳደሪያ ሰነዶችን በስም ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብሎ ፖስታው ላይ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዱ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት በዝቅተኛ ዋጋው መሰረት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ አሸናፊነቱ በተገለፀበት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የሚመጡ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ሥራ ሲገቡ ቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ የተሰረተ የባንክ ዋስትና አልያም ኢንሹራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. ከዚህ በተጨማሪ ይህ ጨረታ በአብክመ ግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ይህን ለማሻሻል ለወጡ አዳዲስ መመሪያዎች መስራት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የሚገዙ አገልግሎቶች እና ግንባታዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሙሉ ስፔስፊኬሽን ፣መመሪያዎጭች እና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅፆችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ፡- ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥና  ንብ/አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 /09 20 25 73 68 በመደወል ማብራሪያ ማኘት ይችላሉ፡፡

የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here