ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ  ከመተሃራ ስኳር ፋብሪካ፣ ከወንጅ /ዴራ/ ስኳር ፋብሪካ ፣ከከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ ከወንጂ /ሸዋ/ ስኳር ፋብሪካ ፣ከአዲስ አበባ እና ከግልገል በለስ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሰቆጣ ዋቢ ዩኒዬን መጋዘን ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር እና ስኳርና የምግብ ዘይት ከአዲስ አበባና ከደሴ በመጓጓዝ  ማስመጣት እና 440 ኩ/ል ቀይ ጤፍ ግዥ በክልል አቀፍ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከሚጓጓዘው የትራንስፖርት (የጭነት) አገልግሎትና የትራንስፖርት ፍቃድ ጋር የተዛመደ እንዲሁም ለጤፉ የብእርና የአገዳ ሰብል ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፡፡ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙትን የትራንስፖርት አገልግሎትና የጤፍ ግዥ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነዱ ሰቆጣ ከተማ ወይብል ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ዋቢ ዩኒዬን ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
  4. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተመስርተው መወዳደር የማይችሉ መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ውል ከተፍጸመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (ሲፒኦ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋቢ ዩኒዬን ገቢ በማድረግ ወይም ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማሰገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም በስተጀርባ ከሚገኘው ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ኃላፊነቱ የተወሰነ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎችህ/ስ/ማህ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ ቆይቶ በአስራ አንደኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይም ከጨረታው ለመውጣት ከፈለጉ የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው (3)ከሶሰት ቀን በፊት በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  10. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህ ኃላፊነቱ የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 11 73 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here