“ዎከር ኤስ2”

0
40

ቻይና ሰራሹ “ዎከር ኤስ2” የተሰኘ ራስ አዘዝ ሮቦት  ካሉት ሁለት ባትሪዎች  ኃይል ያነሰውን  መሙያ ቋት ላይ በመትከል እየሞላ በመተካት የሚሰራውን ተግባር ሳያቆራርጥ ማከናወን እንዲችል  ተደርጐ መመረቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ  አስነብቧል፡፡

በሐምሌ ወር 2025 እ.አ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተው “ዎክር ኤስ2” ሮቦት ኃይሉ የደከመ ባትሪውን በመሙያ ጣቢያ ተክሎ እየሞላ የደከመውን እየተካ የስራ ሰዓቱ ሳያባክን መስራት በመቻሉ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡን ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

 

ቀደምባሉት ዓመታት የተመረቱት ሮቦቶች የባትሪያቸው ኃይል  ሲቀንስ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሙላት ከሚከወኑት ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ቦዝነው መቆየትን ግድ ይላቸው ነበር፡፡ ከዚህ በተለየ በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ባለሁለት እግሩ ሮቦት ካሉት ሁለት ባትሪዎች አንዱ ሲደክም በመሙያ ጣቢያ እየሞላ ስራውን ሳያቋርጥ መስራት ይችላል ሌላኛውን፡፡

 

ሮቦቱ ሀይል ያነሰው ባትሪውን እንደገና ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድበት በመሆኑ ፈጥኖ ወደ ሚከወነው ተግባር መመለስ እንደሚችል ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡ ሮቦቱን ያመረተው ኩባንያ በቅርቡ ባጋራው ቪዲዮ “ዎከር ኤስ2 ሮቦት” ባትሪ የመለወጥ አቅሙን እና ሂደቱን ማሳየት ችሏል፡፡

 

ሮቦቱ ሁለት ባትሪ የሚይዝ ሲሆን  ኃይል ያነሰው ባትሪውን የመሙላት እና የመቀየር  አሰራሩ በኤሌክትሪክ ኃይል ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የተቀፀለ መሆኑንም ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

በመጨረሻም “ዎከር ኤስ2” ሮቦት በብዛት ተመርቶ በቅርቡ ወደ ገበያ እንደሚገባም ነው የተገለጸው።

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የነሐሴ 5  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here