ኪቱሎ ብሔራዊ ፓርክ

0
39

ኪቱሎ ብሔራዊ ፓርክ በምሥራቅ አፍሪካ ታንዛኒያ ደቡባዊ ግዛት ነው የሚገኘው:: የፓርኩ ስፋት 412 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል:: ፓርኩ በሀገሪቱ መንግሥት እውቅና አግኝቶ በ2005 እ.አ.አ ነው የተመሰረተው::

የፓርኩ መገኛ ከፍታ 3,000 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ተለክቷል:: ደን፣ ፏፏቴ፣ ተፈጠሮ አብቅሎ የሚንከባከባቸው የአበባ ዝርያዎቹ መለያ መታወቂያዎቹ ናቸው – ለፓርኩ:: 350 የአበባ ዝርያዎች እንደሚገኙም  ተለይቶ ታውቋል።  በዚህም ኪቱሎ “የእግዚአብሔር የአትክልት ስፍራ” ተብሎ ይጠራል፤ በነባር የአገሬው ኗሪዎች:: በእፅዋት ባለሙያዎች ደግሞ በአበቦች የተንቆጠቆጠው ቀጣና ተብሎ ይጠራል።

 

በፓርኩ ክልል ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ የቢራቢሮ፣ የእስስት፣ የእንሽላሊት እና እንቁራሪት ዝርያዎች አሉት። የ400 ልዩልዩ እፅዋት ዝርያዎችም   መገኛ ነው።

የኪቱሎ ፓርክ መገኛ በአየር ንብረቱ ከዝቅተኛው 14 እስከ ከፍተኛው 18 ዲግሪ ሴል ሺየስ ይለያያል።

ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑም 1600 ሚሊ ሊትር ነው::

 

ወደ ፖርኩ ለመጓዝ በዓየር  ሰንግዌ ዓለም አቀፍ አውሮኘላን ማረፊያ ደርሶ በኪዮሌ ኪያላ አውራ ጐዳና በተሽከርካሪ 125 ኪሎ ሜትር ወይም በምቤያ ከተማ ኢሲዮንጄ ኪቱሎ 67 ኪሎ ሜትር መጓዝን ግድ ይላል::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ታንዛኒያ ስፔሻል፤ ኪዮቶ አፍሪካን ሳፈሪ፣ ታንዛኒያ ፓርክ ድረገፆችን ተጠቅመናል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የነሐሴ 5  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here