የጃፓን ከተሞች ውድመት

0
157

እጅግ ዘመናዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ ስልጠና የነበረው የናዚ ጀርመን ጦር በሶቭየቶች ቀዩ ጦር ተንበረከከ። ጀርመን ሰራዊቷ ክፉኛ ተጎዳ፤ የናዚው ዋና ሰው አዶልፍ ሒትለር ራሱን አጠፋ እና ጀርመን እጅ ለመስጠት ከአሸናፊው ወገን የቀረበላትን ጥያቄ ከመቀበል እና በፊርማዋ ከማረጋገጥ ሌላ አማራጭ አልነበራትም። ይህ ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ለአውሮፓ እስከ 70 ሚልዮን ሕይወት ያስከፈላት አስከፊው ጦርነት ወደ መጨረሻው ምእራፍ መቃረቡን የሚያበስር ተስፋን አነገሰ። ሆኖም አንድ ከባድ  ፈተና ከፊት ለፊት ይጠብቅ ነበር። የጀርመን ዋና አጋር የነበረችውን የሩቅ ምስራቋ ጃፓንን ማሸነፍ የግድ ነበር።

ጃፓን በሰላማዊ ውቂያኖስ ክልል የገነነች ጠንካራ ሀገር ናት። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም ለእንግሊዝና ፈረንሳይ መራሹ ሕብረ ብሄር ኃይል ዋነኛ ተገዳዳሪ ጠንካራ ሰራዊት የገነባች በመሆኗ በቀላሉ ጃፓንን ማንበርከክ የሚቻል አይመስልም ነበር። በመሆኑም የኅብረ ብሔሩ ቡድን አባል ሀገራት ኃይላቸውን አስተባብረው በጃፓን ላይ የአየር ድብደባዎችን ወደ ማድረግ ተሸጋገሩ። ወደ 67 የሚሆኑ የጃፓን ከተሞች የድብደባው ሰለባዎች ነበሩ። ነገር ግን ጦርነቱ ማብቃት አልቻለም። እናም ለስድስት ወራት ጨለማን ተገን አድርጎ በጃፓን ላይ ይደረግ ከነበረው የቦምብ ድብደባ በኋላ በሐምሌ መጀመሪያ 1938 ዓ.ም የሕብረ ብሔሩ ጦር አባል ሀገራት መሪዎች በጀርመኗ ከተማ ተገናኝተው ጦርነቱ በአፋጣኝ የሚያበቃበትን አዲስ መንገድ መከሩ።

የአሜሪካው  ፕሬዝደንት ሐሪ ትሩማን፣ የእንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል፣ የሶቭየት ሕብረቱ ስታሊን ሐምሌ 26 ቀን 1938 (እ.አ .አ) ጃፓን እጅ እንድትሰጥ የሚጠይቀውን የፓትስዳም ዲክላሬሽንን አረቀቁ። ይህ ዲክላሬሽን እንደ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሆኖ የቀረበ እና እጅ የማትሰጥ ከሆነ ግን የኅብረ ብሔሩ አባላት ጃፓንን እንደሚያጠቁ፣ ይህም የጃፓንን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ እንዲደመሰሰ የሚያደርግ እና የጃፓን ምድር ለከፋ ውድመት የሚዳርግ አይቀሬ ውጤት እንደሚያስከትል ያሳስባል።

ጃፓን ከሁለት ቀን በኋላ ምላሿን አሳወቀች።  መንግሥት የማስጠንቀቂያ ሀሳቡን ውድቅ ማድረጉን የጃፓን ጋዜጦች ማስነበብ ያዙ። የወቅቱ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ካንታሮ ሱዙኪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጃፓን መንግሥት የፓትስዳሙን ሰነድ ውድቅ እንዳደረገው ይፋ አደረጉ። የጃፓኑ ንጉሥ ሂሮሂቶ በበኩላቸው የተጠየቀውን ዋጋ ሁሉ ተከፍሎ ጃፓንን ለመከላከል ቁርጥ ውሳኔ አሳለፉ። ጃፓን የመጣው ይመጣል እንጂ እስከፍፃሜ ጠላቶቿን ልትፋለም መሆኑ ለዓለም ግልፅ ሆነ። ቀጣዩ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል ከአሜሪካ በስተቀር ማንም አያውቅም። አሜሪካ በሰው ልጅ ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት ልትፈፅም ዝግጅቷን ጨርሳ ነበር። የሚጠበቀው የጃፓን ምላሸ ነበር፤ ያም አልሆነም ምክንያቱም ጃፓኖች ጥቃት አይወዱም። ምናልባት አሜሪካ አቶሚክ ቦምብ መታጠቋን ቢያውቁ አቋም ይቀይሩ ይሆን? አይታወቅም።

እውቁ ሳይንቲስት አልበርት  አንስታይን በወቅቱ ለነበሩት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አይዘናወር ናዚ ጀርመን አቶሚክ ቦምብ ግንባታ መጀመሯን እና ይህን ቦምብ  ከሁሉ ቀድማ  በእጇ  ካደረገች የአለም እጣ  ፋንታ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል በደብዳቤ ያስጠነቅቃል። በመሆኑም አሜሪካ ይህን ቦምብ ሰርታ ጀርመንን መቅደም እንደሚገባ በሰጠው ምክረ ሀሳብ በመነሳት የአቶሚክ ቦምብ ግንባታው  እንደተጀመረ የታሪክ ማስረጃዎች ያስረዳሉ። እጅግ ከፍተኛ ብሄራዊ ምስጢር ተደርጎ  የተያዘውን የኒኩሌር ቦምብ ግንባታ ፕሮጀክት ማንሀታን  ፕሮጀክት በሚል መጠሪያ ይከናወን ጀመር። ሳይንቲስቶቿ በከፍተኛ ብቃት እና ትኩረት “ትንሹ ልጅ” እና “ወፍራሙ ሰውየ” የሚሉ መጠሪያዎች የተሰጧቸውን ሁለት አደገኛ እና ምህረት የለሽ ኒኩሌር ቦምቦችን ገንብተው እና ሞክረው  አጠናቅቀው ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጀርመን ጦር ተሸነፈ። እናም ለጀርመን ታስቦ የነበረው ጃፓንን  ለማንበርከክ ይውል ዘንድ የአሜሪካው ፕሬዚደንት  ትሩማን ወስነው ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር። እናም የጃፓን የፖትስዳሙን ሰነድ ውድቅ የማድረጉ ዜና ለአሜሪካ ትልቅ አጋጣሚ ነበር። የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ቶሎ ለመቋጨት የሚያስችል ሁነኛ መፍትሄ እንዳላት አሳውቃለች። እናም የተወሰነው ቀን ደረሰ።

ቲኒያን ደሴት ላይ ኢኖላ ጋይ  ይተሰኘ አንድ ቢ-29 ግዙፍ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ነሐሴ 6 ቀን 1945 እ.አ.አ ማልዶ ተነስቶ ወደ ሰሜን አቅጣጫ  ወደ ጃፓን መክነፍ ጀመረ። አንድ ሌላ ቢ-29  አውሮፕላን አጅቦት ተነስቷል። ኢላማው የሒሮሽማ ከተማ ነበረች። ከተማዋ እስከ 300ሺ ነዋሪዎች እንደነበራት  እና  43ሺ ወታደሮችን የያዘች  ወሳኝ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላት ዋነኛ የኢንዱስትሪ ማእከል ነበረች። ለዚህም ነበረ  የጥቃቱ ዒላማ ሆና የተመረጠችው።

ኢኖላ ጋይ የተሰኘውን አውሮፕላን በዋና ፓይለትነት ያበር የነበረው ኮሎኔል ፓውል ቲቤትስ ወደ ኢላማው እስኪጠጋ ድረስ  በዝቅተኛ ከፍታ ላይ  ሲበር ነበር። ወደ ኢላማው ቀረበ፤ እናም የአውሮፕላኑን ከፍታ 31 ጫማ ላይ ጨመረ፣ እናም 8፡ 15 ሲል ግዙፉ አውሮፕላን የያዘውን ቦምብ በሂሮሽማ እምብርት ላይ ለቀቀው። 9ሺ 700 ፓውንድ የሚመዝነው አቶሚክ ቦምብ ቁልቁል ወረደ። ፓይለቱ ቲቤትስ ወዲያው የፍንዳታው ንዝረት  እንዳያገኘው ከቦታው ለመራቅ  ሸመጠጠ። ከአርባ ሶስት ሰከንድ በኋላ “ትንሹ ልጅ” ፈነዳ። እጅግ ከባድ ፍንዳታ የማለዳውን የሒሮሽማ ሰማይ በእሳት እቶን ሸፈነው። ምንም እንኳ ቦምቡን የጣለው አውሮፕላን አስራ ሁለት ማይል ያህል ርቆ የነበረ ቢሆንም የፍንዳታው ንዝረት ንጦታል። አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የበረራ አባላት ዞረው ወደ ከተማዋ ተመለከቱ። ፓይለቱ ቲቤትስ ሀጁኔታውን ሲያስታውስ፣ “ከተማዋ በአደገኛው ደመና ተሰውራለች…ወደላይ ተነነች፣ የጅብጥላ አይነት ቅርፅ በመስራት በሚያስፈራ ሁኔታ በረጅሙ ወደ ሰማይ ቀጥ ብሎ ይወጣ ነበር።”

ቦምቡ ከፈነዳበት ስፍራ በአንድ ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ያለ  ሕይወት ወዲያው በሀይለኛው እሳት ተቃጥሎ ከስሎ ሞተ። ሕንፃዎቹ እና ቤቶች ሁሉም ወደ  አመድነት ተለወጡ። በሰማይ የሚበሩ አእዋፋት በሰማይ ላይ እንዳሉ  በእሳቱ ረገፉ። የጃፓናውያንን ተስፋ፣ ደስታ እና ህልም ያጨለመ  መዓት ከተማዋን ወደ ፍርስራሽነት ለቅፅበት ቀየራት። በቀላሉ ሊገለፅ የማይችል የሞት ፅልመት ዋጣት። መቅሰፍት የሆነ ዓለም አይታው በማታውቀው አውዳሚ ቦምብ ተመታች። ሳይንስ ዳይሬክት የተሰኘው የጃፓን ሙሁራን ጆርናሎች የሚታተሙበት ድረ ገፅ እንደዘገበው። ሂሮሽማ ላይ የፈነዳው ቦምብ ከፍተኛ መጠን ያለው እና  እጅግ አደገኛ ገዳይ ጨረር ነበረው። ከሰባ እስ ከሰማኒያ  ሺህ የሚሆኑ የሄሮሽማ ኗሪዎች ወዲያውኑ ሞቱ። በከተማዋ ውስጥ  የነበሩት 90 በመቶ የሚሆኑት ዶክተሮች እና 93 በመቶ ነርሶች ሞተዋል ወይም  ቆስለዋል። አሜሪካውያን ቦምቡ የከተማዋን 12 ስኩዌር ኪሎሜትር ያህል ስፋት አውድሟል ሲሉ፣ ጃፓኖች በበኩላቸው 69 በመቶው የከተማው ሕንፃዎች እንደወደሙባቸው አምነዋል። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ያለምንም ልዩነት ሰዎችን በጅምላ ለመግደል እና ለማውደም ጥቅም ላይ ሲውል ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በቦምቡ ጥቃት የደረሰው ትክክለኛው የሞት መጠን ከ90ሺህ እስከ 166ሺህ ሰዎች ይገመታል።

ከዘግናኙ የሄሮሽማ ድብደባ በኋላ የጃፓን ባለስልጣናት ውሳኔ አሁንም አልተለወጠም። በዚህ የተናደዱት ፕሬዝደንት ትሩማን፣ “አሁንም ማስጠንቀቂያችንን ካልተቀበሉ፣ ምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ የጥፋት ዝናብ ከሰማይ እንደሚወርድ ይጠብቁ።” በማለት አስጠነቀቁ። ጃፓን በዝምታዋ ገፋችበት። የአሜሪካው ፕሬዝደንት  ትሩማን “አሁንም ማስጠንቀቂያችን ተቀብለው እጅ የማይሰጡ ከሆነ፣ በምድር ላይ እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ አይነት የጥፋት ዝናብ እንደሚወርድባቸው ይጠብቁ።” በማለት ደግመው አስጠነቀቁ።

በሳልስቱ ሌላ ቢ-29 አውሮፕላን ወደ ጃፓን ሌላኛዋ ከተማ አቀና፡፡ እናም ናጋሳኪ በተመሳሳይ ቦምብ ነደደች። እስከ 40ሺህ ሰዎች ወዲያውኑ አለቁ።  ከዚህ በኋላ ነበር ጃፓን እጅ የሰጠችው።

እነሆ ይህ አስደንጋጭ ታሪክ ከተከሰተ 80ኛ ዓመት ሞላው።  ጃፓን ከኒኩሌር የፀዳ ዓለም እንዲፈጠር ያስተጋባ የመታሰቢያ በዓል አድርጋለች።

ሳምንቱ በታሪክ

ጎርቫቾቭ

በሶቭየት ሩሲያ መንግሥት ውስጥ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ኮሚኒስቶች መፈንቅለ መንግሥት አድርገው ነበር። በዚህ መፈንቅለ መንግሥትም ሚካኤል ጎርባቾቭን ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ከስልጣን አስወግዷቸው ለሰአታት የቆየ ክስተት በሩሲያ ታሪክ ውስጥ የተከሰተው ነሐሴ 13 ቀን 1982 ዓ.ም ላይ ነበር። መፈንቅለ መንግሥቱ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሲከሽፍ የሩሲያ ዲሞክራሲያዊና ሪፎርሚስቱ ቦሪስ የልሲን ደግሞ የሩሲያን ሕዝብ በሰልፍ እያስተባበረ ነበር። ከዚያም ቦሪስ የልሲን በሀገሪቱ ቁልፍ መሪ ሆነዋል። ብዙም ሰይቆይ የኮሚኒስት ፓርቲው ታገደ እና ከወራት በኋላም በታሕሳስ ወር 1983 ዓ.ም ሶቭየት ሩሲያ ራሷተበታተነች። በተያያዘም 42ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን የተወለዱት ነሐሴ 13 ቀን 1932 ዓ.ም በአርካንሳስ ግዛት፣ ሆፕ ከተማ ክሊንተን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሕይወት ያልነበሩ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ናቸው።

ምንጭ -ሂስትሪፕሌስ

 

ይድነቃቸው ተሰማ

ስሙ የሚነሳው በታሪክ ለማስታወስ ብቻ አይደለም። በዜና እና በእግር ኳስ ትንተና ፕሮግራሞች ውስጥ ሁሉ ስሙ ይነሳል። ድል የራቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ‹‹በእሱ ጊዜ ቀረ›› ለማለት ይመስላል የስፖርት ጋዜጠኞች የዚህን ሰው ስም በተደጋጋሚ ያነሳሉ። ይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ!

(መሰረት ቸኮል)

በኲር የነሐሴ 12  ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here