ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
37

ለአብክመ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ግዥ የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው በመደበኛ በጀት ለቢሮው የመኪና አገልግሎት የሚውል  በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና በዘርፋ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ ፖስታ ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ዋጋ በመክፈል ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ  በሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ. ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 8:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 በ16 ተኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሙሉ በሙሉ ማንበብና ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 97 04 በሥራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤

አድራሻ፡- ባ/ዳር ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ  ፊት ለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ይገኛል፡፡

የአብክመ ሴ/ህ/ጉ/ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here