በአፈ/ከሳሽ እነ ባንቻየሁ የኔው እና በአፈ/ተከሳሽ ተገኘች አሊ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 በምሥራቅ ወርቅነሽ በምዕራብ መንገድ ፣ በሰሜን ወርቅነሽ እንዲሁም በደቡብ ይርሳው የተዋሰነው በወ/ሮ እመቤት ተሰማ ሥም ተመዝግቦ የሚገኝ የድርጅት ቤት ፤ ስፋቱ 201.638 ካ.ሜ የሆነ ፤በመነሻ ዋጋ 2,036,552 (ሁለት ሚሊዮን ሰላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሀምሳ ሁለት ብር) ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀን ቆይቶ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ በቦታው ተገኝታችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት