የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ 

0
96

በአፈ/ከሳሽ እነ ባንቻየሁ የኔው እና በአፈ/ተከሳሽ ተገኘች አሊ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ  በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኝ በሰሜን የአሰፋ ቤት፣ በደቡብ ካሰች፣ በምሥራቅ መንገድ እና በምዕራብ ብልጫ የሚያወስነው በሟች ደሳለው ተሰማ ሥም የተመዘገበና ለኢንዱስትሪ ዘርፍ አገልግሎት የተመደበ ሆኖ ለተመደበለት አገልግሎት ዘርፍ ማሰማራት እስከሚቻል የስመ-ንብረት ዝውውር የሚቆይ በመነሻ ዋጋ 3,976,575 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ሆኖ  የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀን ቆይቶ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ በቦታው ተገኝታችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here