ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

በአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ  በከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት እና ለምዕራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ አመታዊ የቢሮ፣ የሽንት ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት ወይም ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ግዥ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥውን ለመፈጸም (አመታዊ) ውል በመያዝ (አገልግሎት) ማግኘት ይፈልጋል፡፡  ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ አመታዊ የቢሮ፣ የሽንት ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሰፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27/28 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በቢሮዉ ገንዘብ ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ማስያዝ  አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በ2 ፖስታ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከተማ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፤ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /058 226 61 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ያለምንም ሥርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፤ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፤ በአጋጣሚ የተሰረዘ ከሆነ የተሞላውን ዋጋ የሞላው ድርጅት ከተሰረዘው ቦታ ባጠገቡ መፈረም አለበት፡፡

የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here