ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
50

የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን በደብረ ብርሃን፣ ጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞች የሚገኙ የትራፊክ ኮምፕሌክስ የካሜራ ተከላ የሚያስፈልጉ እቃዎችን በማቅረብ የካሜራ ተከላ እና ኔትዎርክ ዝርጋታ ሥራ (የአገልግሎት) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች  መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ አግባብነት ያላቸው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ስለሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የዕቃ እና አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ለእያንዳንዱ ከተማ ለዕቃዎች፣ የካሜራ ተከላ እና ኔትዎርክ ዝርጋታ ሥራ (የአገልግሎት) ዋጋ በጠቅላላ ዋጋ ድምር ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ  ትራንስፖርትና  ሎጅስቲክስ ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here