በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የምሥራቅ በለሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛው በጀት በምሥራቅ በለሣ ወረዳ ሥር ላሉ መኪና ላላቸዉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል አመታዊ የመኪና እቃዎችን (መለዋወጫ) እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የሚቆይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዉል በመስጠት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም መወዳደር ለምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ በለሣ ወረዳ ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን የጨረታው መሥፈርትም፡-
- በዘርፉ የታድሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርትፊኬት (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ ሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 0.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው የሚገቡትን ውለታ በአግባቡ የሚፈጽሙ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኢቨሎፕ ጨረታዉ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ለ15 ቀን በጋዜጣ ወቶ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይክፈታል፤ እንዲሁም ተጫራቾችና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የታዘዘው የመኪና እቃ በበጀት እጥረት ምክንያት አንሶ ሳይገዛ ቢቀር ጽ/ቤቱ የማይገደድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን በዓል (ካላንደር) ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የቅሬታ ቀን ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞሉት ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ድርጅት ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ ምሥራቅ በለሣ ወረዳ ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 339 00 04 /01 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ25 ተከታታይ ቀናት ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ድርጅቱ ጨረታዉ ሲከፈት ከፖስታዉ ላይ ማህተሙን፣ ሥም እና ፊርማዉን ማስቀመጥ አለበት፡፡
- የሚገዙት (የሚቀርበዉ የመኪና መለዋወጫዎች) አሸናፊዉ ድርጅት እስከ ጎንደር ከተማ ጋራጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የሚቀርቡት እቃዎች በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸዉ፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፋቸዉን እቃዎች ጽ/ቤታችን በሚፈልግበት ጊዜና ቦታ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወዲያዉኑ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የምሥራቅ በለሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት