ለማተሚያ ማሽን መፈብረክ ፈር ቀዳጁ

0
40

ጀርመናዊው የወርቅ አንጥረኛ ጆሃንስ ጉተንበርግ በ1436 እ.አ.አ ጽሁፍን በወረቀት ላይ የሚያትም ማሽን መስራት የጀመረበት ዓመት ነበር፡፡

ከአራት ዓመታት በኋላም የማሽኑን መሰረታዊ ተንቀሳቃሽ ክፍሎች ገጣጥሞ የመጀመሪያ ስሪቱን ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

ጉተንበርግ በ1454 እ.አ.አ ማተሚያ ማሽኑን ለንግድ ስራ አዋለ፤ በዚያው ዓመት42 ገፅ ያለው ሀይማኖታዊ ጽሁፍንም ለህትመት ማብቃት ችሏል፡፡

የጉተንበርግ ማተሚያ ማሽን በሌሎች በርካታ ግኝቶች እና ፈጠራ እየተሻሻለ ከአዝጋሚ አሠራር ተላቆ በተቀረጹ የተነጣጠሉ ፊደላትን በመገጣጠም የሚፈለገውን ጽሁፍ መፃፍ ያስቻለ ነበር፡፡ ለጽሁፍ የሚሆነውን ቀለም ራሱ ጉተንበርግ በዘይት ላይ ተመስርቶ መስራትም ችሏል፡፡

ጉተንበርግ ከብረት በተቀረጹ ፊደላት ላይ የዘይት ቀለሙ ነክቷቸው ወይም ተቀብተው ወደታች ወረቀቱ ላይ ሲጫናቸው ጽሁፉን ወረቀቱ ላይ በሚፈለገው መልኩ ማስፈር በመቻሉ በጊዜው ተወድሷል፤ ተደንቋል፡፡

ይኽው ፈጠራ እና ስልት ቀደም ብሎ በእጅ ጽሁፍ ከሚሰሩት  በበለጠ ፍጥነት ህትመትን ለማከናወን አስችሏል፡፡

የጉተንበርግ የመጀመሪያ የማተሚያ ማሽን ስራ የመረጃ አብዮት “Information revolution’’  አሀዱ ማለቱን ልብ ይሏል፡፡

ምንጭ፡- ኤስ ሲ ኤ አረ ሲ ላይብረሪ ኦሪጐን ኢዱ  እና ብሪታኒካ ድረ ገጽ፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here