በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጋዜጣ “ዓዕምሮ” በ1900 ወይም በ1901 ዓ.ም ነው የተጀመረው:: ጋዜጣው አራት ገፆች ነበሩት:: በሣምንት አንድ ጊዜ ቅዳሜ ነበር ህትመቱ:: ጋዜጣው በእጅ ተገልብጦ በ24 ቅጂ ይሰራጭም ነበር- ለቤተመንግሥት ቅርብ ለሆኑ መሣፍንት እና መኳንንቱ::
በጋዜጣው ሽፋን የሚያገኙት ወይም ትኩረት የሚደረግባቸው በቤተመንግሥት ዙሪያ የሚከናወኑ እና ሀይማኖታዊ ሁነቶች ነበሩ::
በ1905 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባ በተከፈተው ማተሚያ ቤት እየታተመ የጋዜጣው ቅጂ ብዛት ከ200 በላይ ደርሶ ነበር:: በ1906 ህትመቱ እስከ ተቋራጠበት ጊዜ ድረስ::
ኋላም ህትመቱ እንደገና ቀጥሎ ከ1924 እስከ 1935 ዓ.ም ወቅታዊውን የአውሮፓውያን አገራት ግንኙነት እና የኢትዮጵያን አንድነት የሚሰብኩ፣ የንጉሳዊ ቤተሰቦች ጋብቻ እና ልደት ወ.ዘ.ተ ሲስተናገዱበት ቆይተዋል::
ከሐምሌ 1935 ዓ.ም በኋላም ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር የነበራትን ምኞት የሚያጋልጡ ጽሁፎች ለንባብ በቅተውበታል- በዓዕምሮ::
ምንጭ ፡- ሊንክዲን ድረ ገጽ፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም