በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማው ለሚሠራው የአደባባይ ግንባታ ጨረታ መጫረት የምትችሉ ደረጃ 7 በላይ ተጫራቾች መጫረታ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመልስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 12 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ወጭ ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማዕደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስገሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ60 ቀን ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት