በምዕራብ ጐንንደር ዞን የዳሞት የገ/ሁሉ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የት የ2017 ዓ.ም ምርት ዘመን ነጭ በቆሎ ሎት 1 – 5,000 ኩ/ል ሎት 2 – 5,000 ኩ/ል ሎት 3 – 10,000 ኩ/ል በተጨማሪም ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የG+5 ለህንጻ የሚያስፈልጉ እቃዎች ማለትም ሎት 1 ፈርንቸር ከነመገጣጠሙ፣ ሎት 2 የመጋረጃ ቁሳቁስ ከነጁ፣ ሎት 3 የሳውንድ ሲስተም እስከመገጣጠሙ እና ሎት 4 ላይት ቦክስ (ዲጅታል ታፔላ) እስከመገጣጠሙ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸዉና እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የጨረታው ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ እና የሚሞሉት ዋጋ የቫት ግብይት ከሆነ ከነቫቱ መሆን አለበት፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1/ሂሳብ ክፍል እስከ መጨረሻው ቀን 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለበቆሎ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለG+5 ህንጻ እቃዎች በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ሥም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፤ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃየተ ቡሬ 03 ቀበሌ ከሚገኘው ዋና ቢሮ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
- በቆሎ የማንሻ ቦታ ቡሬ 04 ቀበሌ ሆኖ የ10,000 – 30 ቀን 5000 ኩ/ል በየራሱ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
የዳሞት የገ/ሁሉ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃየት