ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
25

በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር የኦዲት አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መጋረጃ እና ጄኔሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/  ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒዮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመግዛት ጠቅላላ ዋጋ /ታክሱን ጨምሮ/ በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት 10 በመቶ ውል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  8. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0934879762 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዊ ልማት ማህበር

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here