ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
17

በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት  በሆስፒታሉ ውስጥ ተመድበው ለሚሰሩ ሰራተኞች እስከ 61 ሠው የሚጭን የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ብዛት 2 የሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፤ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባችው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የኪራይ ሥራ ዋጋ ድምር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤ መ/ቤቱ ቫት ይሰበስባል፡፡
  6. ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት ሥራዎች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  7. ተጫራቾች የሞሉትን የሥራ ዋጋ 2 በመቶ በጨረታ ማስክበሪያ (ቢድ ቦንድ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በማስያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከነሀሴ 26/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 17/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ22 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ ነሀሴ 17/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚህ  ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በሥራ ሂደቱ ሥልክ ቁጥር 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  17. የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  18. ውድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
  19. የመኪና ሥራ ወጭ ለሹፌር፣ ለነዳጅ በተመለከተ እና ሌሎች የሚያስፈልጉ ወጭዎች  አሸናፊው ይሸፍናል፡፡
  20. አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው ቦታ ደርሶ መልስ ሰርቢስ መስጠት አለበት፡፡
  21. አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ሆ/ሉ ሥራ ብሎ ሲያዘው በታዘዘው ቀን ውስጥ የሰራተኞች ሰርቢስ መስጠት አለበት፡፡

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here