ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
67

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነብሴ ሣር ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለእነብሴ ሣር ምድር ወረዳ ዉሃ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለዶማ /08/ ቀበሌ መጠጥ ዉሃ ለGCF ፕሮጀክት ፕሮግራም አገልግሎት የሚዉሉ ፓምፕ፣ ፓወር ኬብል፣ የመገጣጠሚያ ዕቃዎች እና የተከላ ሥራ ሁሉንም ራሱ ችሎ በዘርፉ የሥራ ፈቃድ ያላቸዉን አወዳድሮ አሸናፊን ለይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎች ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ ተቋራጭ ደርጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሚሞሉት ዋጋ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች ሰነድ በሚመልሱበት ወቅት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም  በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ፣ ፊርማና ማህተም በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥራቅ ጎጀም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ሆኖ እንደ ተጫራቾች ምርጫ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ጥሬ ገንዘቡን በመሂ/1 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ያላቸዉን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ አንድ ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በሥልክም ሆነ በአካል አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ  መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ባለ 4 ገጽ የሥራ ዝርዝር የተያያዘ መሆኑን ተጫራቾች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ  በእነብሴ ሣር ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥልክ ቁጥር 058 666 04 14 /00 03 /በመደወልና በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here