በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳዳር የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ የፕስትሪ ሶፍትዊር ለመጫን እንዲሁም ኮምፒዉተሮቹን ለማገናኘት የኔትወርክ ዝርጋታ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራትና ማስጫን ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀቱ ጋር (Payer ldentificain NuMber) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን የጨረታ ማስገቢያዉና የመክፈቻዉ ሰዓትና ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ የሥራ ስዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸዉና በታወቁ ባንኮች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን ኮፒ በማድረግ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 2 ቀን በፊት በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታ ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታዉን ካሸነፉ ለዩንየኑ ሰራተኞች ስልጠናዉን በ15 ቀን ዉስጥ ሰምተዉ ከጨረሱ በኋላ የባለሙያዎችን አቅም የበለጠ ለማዳበር ለ3 ወር የኦን ላይን ስልጠና የሚሰጡ መሆኑን ጭምር መገንዘብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ የገ/ህ/ስ/ማህበር ዩኒየን ኃላፊነት የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401173 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዋቢ ሁለብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ