አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአደጋ ምላሽ ሥራዎች ዙሪያ ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለሥራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ በማህበሩ ዋናዉ መ/ቤት ባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- መግዛት የሚፈልጉ ማንኛዉም ግለሰብ /ድርጅት መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል በአማራ ልማት ማህበር ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 108 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡትን የተሸከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሠነዱ ላይ በማየት በማህበሩ ዋናዉ መ/ቤት እና አዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት በአካል በማየት ዋጋዉን በዋጋ መሙያ ቅጽ መሠረት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራች ድርጅቶች የሚያቀርቡት የተሸከርካሪ ዋጋ ከመነሻ ዋጋ ማነስ የለበትም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ዋጋ የሞሉ ተጫራቾች ከዉድድር ዉጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ በሚቆጠር በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ዉል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማህበሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር(አልማ)