የአማራ ክልል እንቅስቃሴ ጉዳተኞች ማህበር በአብክመ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 194/2004 አንቀጽ 63/1/ መሠረት በፈቃድ ቁጥር 094 የተመዘገበ ሲሆን ስያሜውና ዓርማ /ሎጎ/ ተመዝግቦ ህጋዊ እውቅና እንዲሰጣቸው በቁጥር አ/አ/ጉ/ማ 0030/17 በሆነ በ16/12/2017 ዓ/ም በተፃፈ ማመልከቻ ጠይቀዋል፡፡ ስለሆነም ማህበሩ እንዲመዘገብ የቀረበውን ዓርማ /ሎጎ/ በክልሉ መመዝገቡ የሚቃወም ካለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት መቃወሚያውን አብክመ ፍትሕ ቢሮ የሰነዶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 እንዲቀርቡ እያሣወቅን እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ካላቀረቡ ግን ማህበሩን የምንመዘግብ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ