የጎሃ በጎ-አድራጎት ማህበር ለወረባቦ ወረዳ ፍትህ ጽህፈት ቤት ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት የጎሃ በጎ-አድራጎት ማህበር በህግ እዉቅና ያገኝ ዘንድ በጽ/ቤታችን እንዲመዘገብላቸዉ ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም የጎሃ በጎ አድራጎት ማህበር ከመመዝገቡ በፊት የጎሃ በጎ-አድራጎት ማህበሩን ስምና የመለያ አርማ (ሎጎ) የሚቃወም አካል ካለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-3 በመቅረብ ተቃዉሞ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተቃውሞ ካልቀረበ እውቅና የሚሰጠው መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ወረባቦ ወረዳ ፍትህ ጽህፈት ቤት