ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት አመት በዞኑ ሥር ለሚገኙት መምሪዎች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እና ሎት 2 የመኪና ጎማ እቃዎችን በግለጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከሰሜን ጎንደር ዞን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከጳጉሜ 03/2017 እስከ መስከረም 12/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1  መስከረም 13/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ  በ4፡30 የከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን የሚያቀርበው  ዞኑ የመኪና የእጅ ዋጋ ካሸነፈበት ጋራዥ ሲሆን  በወቅቱ የሚፈለጉትን  መለዋወጫዎች እንዲቀርቡ ተቋሙ በደብዳቤ ትዕዛዝ በሚሰጥበት ወቅት ንብረቱን በአካል በማቅረብ ለሰ/ጎ/ዞን ንብረት ክፍል  የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፤ የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 417 25 44 /058 417 01 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here