በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከተማው መጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ የቧንቧና የመገጣጠሚያ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ደብረ ኤልያስ ከተማ ውሃና ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የእቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ11:00 ይዘጋና በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን መ/ሂ1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፤ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በመ/ቤቱ በመሂ/1 ወይም (በሲፒኦ) በባንክ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የንግድ ፈቃድና የቲን ምዝገባ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በመያዝ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈልበት 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰነዱ ላይ በተቀመጠው ስፔስፊኬሸን መሰረት ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ከነዚህም በተጨማሪም እቃውን በሚያቀርቡበት ወቅት ጽ/ቤቱ ባቀረበው ሳንፕል መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ያሸነፈውን እቃ የደብረ ኤልያስ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማስረክብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጋችሁ በስልክ ቁጥር 058 250 00 03 ፣09 10 02 27 60 ፣09 20 51 31 86 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውድድሩ በጥልቅ ወይም በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የደብረ ኤልያስ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት