በአ/ፈ ከሳሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ. ሙሉቀን ዘውዴ ፣ 2ኛ. ደረጀ አድማስ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ፤ በ1ኛ. አፈ/ተከሳሽ ሙሉቀን ዘውዴ ስም የተመዘገበ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኝ በሰሜን አለነ ደርጌ፣ በደቡብ አስረሳች ከበደ፣ በምስራቅ ክፍት ቦታ እና በምእራብ መንገድ የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 2,652,691.1 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከአንድ ሳንቲም/ ሳይጠብቅ፤ የጨረታ ማስታወቂያው መስከረም 5/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በእንጅባራ ከተማ አስ/ቀበሌ 01 አስተዳደር ግቢ ውስጥ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የምትፈልጉ በቦታው በመገኘት መወዳደር ትችላላችሁ፤ የጨረታው አሸናፊ ወዲያውኑ የጨረታውን ¼ኛውን የሚያሲዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ /ፍ/ቤት