ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

በማዕክላዊ ጎንደር በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ከመስከረም 26 ቀን 2018 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ድረስ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውል ደረጃ አንድ ኮስትር መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዓቃቢ ህግ ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. መኪናው የሚፈልጋቸውን ወጭዎች ከናፍጣ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ባለንብረቱ (ባለሃብቱ) የሚሸፍን
  5. ከመስከረም 26/2018 እስከ ሰኔ 30 /2018 ዓ/ም ድረስ ውል ሊወስድ የሚችል፡፡
  6. የመኪና ሊብሪ ያላቸው ሆኖ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ዋጋ በሞላ ተወዳዳሪ አሸናፊዉን የሚለይ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾ በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ክማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረበ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፤ ጨረታው ከመስከረም 05/2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 19/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  9. የጨረታው ሳጥኑ የሚታሸገው መስከረም 19/2018 ከቀኑ 11፡30 ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት በሳንጃ የመ/ደ/ሆስፒታል አዳራሽ በ20/01/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ይሆናል፤ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናልና ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  15. ሆስፒታሉ የሚገኘው ሰርቢስ ከሚጀምርበት ቦታ ጀምሮ 3 ኪሎ ሜትር እርቀት አለዉ፡፡ በመሆኑም ጠዋት 1፡50 ወደ ስራ ፣ለምሳ 6፡30 ከምሳ መልስ 8፡20 እንዲሁም ማታ ወደ ቤት 11፡30 በድምሩ 4 /አራት ዙር እና እሁድና ቅዳሜ 2፡30 ወደ ቢሮ 11፡30 ወደ ቤት በድምሩ ሁለት ዙር ማመላለስ አለበት፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለዋስትና የሚያዘው (ሲፒኦ) በቁጥርና በፊደል የተጻፈው የተለያየ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 19 85 88 /09 39 24 50 07 /058 273 03 94 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here