“ኢትዮጵያዊያን አይበገሬ ናቸው!” – ፔትሮ ሳሊኒ

0
137

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 04 ቀን 2017 ዓ.ም የምረቃ ሥርዓ ተበስሯል፤ በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የጣሊያኑ ሳሊኒ (ዊ ቢውልድ) ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ ኢትዮጵያዊያንን ኤበገሬ ሲሉ ነው ያወደሷቸው::

የግድቡን መጠናቀቅ በተመለከተ ሲናገሩም “ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ሆነ። የእኔ እና የኢትዮጵያ ሕልማችን እውን ሆነ። ከዚህ በላይ ምን የሚያኮራ ስኬት ይኖራል!” ነው ያሉት።

“የግድቡ ፕሮጀክት ደኅንነት የነበረው ፕሮጄክት መሆኑን ያነሱት ሳሊኒ ታላላቅ ስኬቶች ዋጋ እንደሚከፈልባቸው ሁሉ በግድቡ ግንባታ ሂደትም የሰው ዋጋ እንደተከፈለበት አክለዋል። ለአብትም በግንባ ሂደቱ 33 የድርጅቱ ሠራተኞች በመንገድ አደጋ እና በሌሎች ምክንያቶች ሕይወታቸውን እንዳጡ አንስተዋል።

25 ሺህ ወጣቶች በሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደተሰጣቸው በማሳት ይህም በቀጣይ ለኢትዮጵያ መሠረታዊ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ፔትሮ ሳሊኒ የግድቡን መሠረት ከጣሉት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በቅርበት መሥራታቸውን ተናግረዋል። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም “’ለሀገሬ ሕልም አለኝ፤ የተትረፈረፈ የኃይል ሉዓላዊነት። ዓባይ ላይ ፕሮጀክት ልትነድፍልኝ ትችላለህ? በፍጥነት ሥራው አለኝ” እንዳሏቸው ገልፀዋል።

በግድብ ግንባታ እርሳቸው እና ቤተሰባቸው የቆዬ ትስስር እንዳቸው የተናገሩት ሳሊኒ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ በብዙ ፈተና ውስጥ ተከባ እንደገነባች ነው የጠቀሱት።

“ሀገሪቱ ይህንን ግድብ እንድትገነባ ማንም አልፈለገም። ማንም ገንዘብ ለማቅረብ አልፈለገም። ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮች፤ ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ መፍትሔው ቀላል አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ችግርን አይፈሩም። አይበገሬዎች ናቸው። ችግር እና ጠላት ሲገጥማቸው አንድነታቸው ይጠብቃል፤ ጥረታቸውንም በእጥፍ ይጨምራሉ:: እናም ማግኘት ያለባቸውን ያገኛሉ” በማት ነው ያደነቁት፡፡

 

(ጌትሽ ኃይሌ)

በኲር የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here