ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
57

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ግዥዎች ማለትም ሎት 1 የጥበቃ ሥራ አገልግሎት ሎት 2 የጽዳት ሥራ አገልግሎት፣ ሎት 3. የነዳጅ ግዥ እና ሎት 4 የጭነት አገልግሎት ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የአንድ ጊዜ የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት ሎቶች በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ግዥዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን ብር 50 (ሃምሳ ብር) ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጥበቃ እና የጽዳት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አመታዊ ግዥዎች ጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ የነዳጅ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 የጭነት አገልግሎት ብር 5,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ስም ማስያዝ አለባቸው
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፤ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታው የጥበቃ እና የጽዳት አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የአመቱን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የነዳጅ የዉል ማስከበሪያ ብር 50,000 የጭነት አገልግሎት ብር 20,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም አገልግሎት እና እቃዎችን ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ ከግዥዉ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፤ የተሻለ ዘዴ ካገኘም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በፋክስ ቁጥር 058 775 13 32 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 00 16 /00 63/ 1016 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here