ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
51

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመኪና እቃ፣ ማኒፋክቸሪንግ ኤሌክትሪክሲቲ፣ ኮንስትራክሽን፣ አይቲ ጋርመንት እና ለመሰረተ ልማት ግንባታ አገልግሎት የሚዉሉ ጥሬ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር 100,000 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የሚስጥር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የሥራ ዝርዝሩን ዓይነት ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ዉድድሩ በነጠላ ድምር ዋጋ ሆኖ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ የሚሆን ነዉ፤ ተጫራቾች ያሸነፉትን ድርጅት እቃዎችን በራሱ ወጭ በማጓጓዝ በባለሙያተኞች እየተረጋገጠ ዕቃዎችን ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከመስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 እንዲሁም ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል በጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡05 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)ነው፡፡
  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ቁጥር 058 111 83 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here