ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ               

0
29

    በደቡብ ጎ/ዞን የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል APTS/AUDITABLE PHARMACUTICAL TRANSACTIONS SERVICE/ የአለሙኒየም ስራ በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡
  4. ግዡ ከ200,000 / ከሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  5. ከአሁን በፊት APTS/ AUDITABLE PHARMACUTICAL TRANSACTIONS SERVICE/ ስራ መስራቱን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሙሉ ቁሳቁሶችን ራሳቸው በማቅረብ መስራት የሚችሉ፡፡
  7. የንግድ ፈቃድ አይነት  የአልሙኒየም ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በእ/የመ/ደ/ሆ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ ውስጥ  አድርጎ እመደሆ  በተዘጋጀው የጨረታ  ሳጥን ውስጥ ማስገባት  አለባቸው፡፡
  11. ሆስፒታሉ የሚያሰራውን ስራ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን የስራ አይነቶች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው አንድም ስራ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  13. የሚሰሩትን የስራ አይነቶች /ስፔስፍኬሽን/ መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  15. ሆስፒታሉ አሸናፊውን በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ይመርጣል፡፡
  16. ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በቀጣዩ በስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  17. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስትሞሉ ስርዝ ድልዝ (በፍሉድ) የጠፋ መኖር የለበትም ፡፡
  19. አሸናፊው ተጫራች በስሙ የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት፤ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  20. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስም በባንክ በተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
  21. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  22. በተለያዩ ምክንያቶች የጨረታ ሰነዱ ችግር ቢኖርበት ማሰታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር)ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስተካከያ የሚደረግበት ይሆናል፡፡
  23. በዚህ ሰነድ ያልተገለፀ ሀሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  24. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ፡፡በስልክ ቁጥር 0584400913 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here