ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
26

የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የግቢ ውበትና የቢሮ ጽዳት አገልግሎትና የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ ፤በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የተሽከርካሪ ጥገና 3,000.00 /ሶስት  ሺህ ብር/ ዓመታዊ የግቢ ውበትና የቢሮ ጽዳት አገልግሎት 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል የገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማለትም ከ26/1/2018 እስከ 10/2/2018 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ተኛው ቀን በ 11/ 2 /2018 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. በሚገዙ የዕቃዎች /አገልግሎቶች/ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582263100/ በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡

የአብክመ መንግስት ፍትህ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here