በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና የጽፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጽፈት መሳሪያ የሚቀርበው በተቀመጠው ናሙና መሰረት ሲሆን አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ውጤት ሆኖም የመኪና መለዋወጫ ዕቃ አሸናፊ የሚለየው በተናጠል ዋጋ ነው እንዲሁም የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የአሸነፉበትን የመኪና መለዋወጫ እቃ እና የጽፈት መሳሪያ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ባሉት ንብረት ክፍሎች ማድረስ ወይም ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 ወይም 09 18 73 90 06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡
የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት