ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የአብክመ  የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ ዘመናዊ ጂ+1 /G+1/ ወርክ ሾፕ እና ቢሮ ህንፃ የፊንሽንግ ሥራ፣ የህክምና ግብዓት አቅርቦት፣ የህትመት ሥራ በእያንዳንዱ የሥራ መስክ ህጋዊ የግንባታና የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች እና አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በግንባታ ዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/፣ ተከታታይ ደረሰኝ ያላቸው ፡፡
  3. ለግንባታ ሥራ ከተማ ኮንስትራክሽን እና ልማት ቢሮ የታደሰ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ለግንባታ ሥራዉ ደረጃ 6 እና በላይ መሆናቸዉን የሚያሳይ የታደሰ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ከዚህ በፊት ግራውንድ +1 እና በላይ ግንባታ ሰርተዉ ለማጠናቀቃቸዉ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና ሌሎች በዘርፉ የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የግንባታዉን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በሞሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻዉ በፖስታ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ኢንስቲትዩቱ የከተማ ኮንስትራክሽንና ልማት ቢሮ የግንባታ መመሪያ በሚያዘዉ መሰረት በግንባታዉ ላይ አስፈላጊዉን ማሻሻያ ወይም የለዉጥ ሥራ ሊያሰራ ይችላል፡፡
  11. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የህክምና ግብዓቱ እና ህትመቱ በ16ኛዉ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 3፡35 የሚከፈት ሲሆን የግንባታዉ ደግሞ በ22ኛዉ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 3፡35 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ተወዳዳሪዎች የግንባታ ጨረታ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር)፣ የህትመት ሥራዉን እና የህክምና ግብዓቱን ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለግንባታ ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) ለህክምና ግብዓቱ እና ለህትመት ሥራዉ ብር 5,000  (አምስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ  /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የኢንሹራንስ ጋራንቲ ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  14. የጨረታው አሸናፊዎች የሚለየው የግንባታዉ በመሀንዲስ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቸክ/ መሰረት ሲሆን የህ/ግብዓቱ እና ህትመቱ በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  15. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  17. ኢንስትትዩቱ የሚሰበስበው 3 በመቶ ዊዝ ብቻ ነዉ፡፡

የአብክመ  የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here