የሠራተኛ ሰርቪስ የመኪና ኪራይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና /ፍ/አገ/ ድርጅት አንድ ተሸከርካሪ ሾፌር እና ነዳጅ አከራይ ሸፍኖ ድርጅቶችን ወይም ግለሰቦችን በውስን ጨረታ አወዳድሮ 12 ወር ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ሰርቪስ መከራየት ይፈልጋል። ስለዚህ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ተሸከርካሪውን ማከራየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)  ሰርተፊኬት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  1. ለኪራይ የቀረበውን ተሸከርካሪ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  1. በየወሩ የአገልግሎት ክፍያው ሲፈፀም ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ 20,000.00 (ሃያ ሽህ) ብር ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  1. የሚንቀሳቀሱበት የፌርማታ (ቦታዎች) ቀበሌ 08 (ከዋናው የውሃ አገ/ድርጅት   ተነስቶ በጊወርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ወደ ቀበሌ 13 አየር መንገድ ዘጌ መገንጠያ ወደ ሄደበት ተመልሶ ማድለቢያ፣ገጠር መንገድ ይዞ በቀበሌ 16 ቁልቋል ትምህርት ቤት ቻይና ካምፕ ወደ ቀበሌ 14 አቡነሀራ ገበያ ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲን አስፋልት ወደ ዱዱ 40 ሜትር መስቀለኛ ፣ወደ ባታ ቤተክርስቲያን ደርሶ በሄደበት ተመልሶ ልደታ ታክሲ ተራ ወደ ቀበሌ 14 ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወደ አኮቴት አደባባይ አዲናስ ሆስፒታል ፣ወደ አዝዋ ሆቴል አስፋልት ቀጥታ በፓፒረስ ዋናው ቢሮ መነሻ ቦታ መድረስ ሲሆን በአጠቃላይ ከአባይ ወንዝ ምዕራብ ያለውን አካባቢ ጥዋትና ማታ ሰርቪስ  የሚሰጥ፡፡
  2. ሞዴላቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2014 እና በላይ ያሆኑና፤የወንበር ልብሱ የተሻለ መኪና ለድርጅታችን ለማከራየት የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 222 ገዝቶ በመውሰድ መጫረት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የዋጋ ማወዳደሪያ ፖስታዎች በማሸግ በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 202 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው  ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ቆይቶ በ15 ተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00  ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ለበለጠ መረጃ ባህር ዳር በስልክ ቁጥር 0583207059 መጠቀም ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ ድርጅት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here