በአካል መገጣጠሚያ ላይ በሚገኝ የደም ቧንቧ በሚፈጠሩ ጥቃቅን ኬሚካላዊ ለውጦች የሚከሰት የአሲድ መጨመር እና እብጠትን ለመፈወስ ፀረ ብግነት ቅባት መሰራቱን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል::
በእንግሊዝ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በአካል መገጣጠሚያ አቅራቢያ የሚገኝ የደም ቧንቧ ላይ የሚፈጠር እብጠት እና ህመምን ለማዳን የጐንዮሽ ጉዳቱ ያነሰ ወፍራም ቅባት (ጄል) መስራት ችለዋል::
ወፍራሙ ቅባት በቀጥታ ታካሚዎች ላይ ከመዋሉ በፊት የግምገማ ሙከራዎች እንደሚያስፈልጉ የጠቆሙት ተመራማሪዎቹ ከመገጣጠሚያ የደም ቧንቧ እብጠት ባሻገር “ካንሰርን” የመሳሰሉ ህመሞችን ሊያቀል ወይም የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ሊቀንስ እንዲመችል ነው የጠቆሙት::
የምርምር ቡድኑ መሪ ኘሮፌሰር አረን ሸርማን እንደተናገሩት በቡድኑ ውስጥ በተካተቱት የመድሃኒት ቅመማ ባለሙያዎች የተሰራው ቅባት ከተለያዩ መድሃኒቶች ጋር ተጣምሮ ሊሰጥ ይችላል:: ወፍራሙ ቅባት በውስጡ የተቀላቀለውን መድሃኒት እብጠት እና ብግነት በተስተዋለበት መገጣጠሚያ ለቀናት፣ ለሳምንታት እና ወራት በመልቀቅ ህመሙን ያሽላል ነው ያሉት -::
በወፍራሙ ቅባት ወይም ፈሳሽ ውስጥ የሚሰጠው የመድሃኒት አቅርቦት ሙቀት፣ ጨረርን ከመሳሰሉት በፀዳ መልኩ በአካል የራሱ ስሪት ወይም ተፈጥሯዊ ሂደት ዝውውሩ የሚከዎን መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ነው ተመራማሪዎቹ ያሰመሩበት::
በምርምር ቡድኑ የተዘጋጀው ወፍራም ቅባት ለተለያዩ ህመሞች ማስታገሻ እና ፈውስ ለመሻት አጭር ወይም ረዘም ያለ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውም ቢሆኑ ተገቢውን ሙድሃኒት ቀላቅሎ መስጠት እንደሚያስችልም ነው ያረጋገጡት::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም