የአብክመ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ በ3 ሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት3. የፅዳት ዕቃዎችን መግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም፣አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው የተሳተፈ ማንኛውም ድርጅት ዋጋ ካቀረበ በኋላ ዋጋውን መለወጥና ማሻሻል ወይም በጨረታው አልሳተፍም ቢል ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተመላሽ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሠከረለት (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከተሸነፋ ያስያዙት ቢድ ቦንድ እንዲለቀቅ በጸሁፍ ሲያሣውቁ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ስራ አፈጻጸም ዋስትና ያሸነፋበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ፤በሚቀጥለው 10 ተከታታይ ቀን በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፤ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በገንዘብ ቢሮ እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያዉ ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ካለፈ በኃላ ለ20 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፤ በዚሁ እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ፤ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- መ/ቤቱ የግዥዉን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዋጋ መሙያዉ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች ያልተገለፁ ቢኖሩ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ተገዥ ይሆናል፡፤
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 226 21 51/058 222 ፖ.ሣ.ቁ 1324 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት