ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ የህብረተሰብን ፍላጐት የሚያሟሉና ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን (ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here